የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ መከላከል ተጀመረ

0
251

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወደ ሀገር እንዳይገባ ለመከላከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ሥራ መገባቱን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። የዓለም ጤና ድርጅት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ ከታሕሳስ 21/2012 ጀምሮ በቻይና ዉሃን (Wuhan) ክልል የተከሰተ መሆኑን አሳወቋል።

በቫይረሱም የ17 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ 581 ሰዎች መካከልም 5 መቶ 71 ቻይናዉያን ናቸዉ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቻይና ብቻ አምስት በረራዎችን ወደ ቤጂንግ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ሻንግሃይ፣ ቸንዱና ያደርጋል። በመሆኑም በማንኛውም የአየር መንገድ በኩል ለሚሄዱ መንገደኞች ለቫይረሱ ተጋላጭ እነዳይሆኑ ስለ በሽታው መረጃ መስጠትና ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡት በበሽታው ተይዘው ሊሆን ስለሚችሉ በአለም የጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብ መሰረት ለሁሉም መንገደኞች የሰውነት ሙቀት ልየታ ስራ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መጀመሩን ኢንስቲትዩቱ አስታዉቋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተለያዩ የጥንቃቄ ስራዎችን የጀመረ ሲሆን ለክልሎች እና ለባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን የዝግጅት ስራዎች እንዲያከናውኑ የቅድመ ዝግጅት መልዕክት ማሰራጨቱን በመግለጫዉ ተመላከቷል። የኮሮና ቫይረስ (corona viruses) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል።

በሽታው በጠናባቸው ታማሚዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳንባ ምች (pneumonia)፣ ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም የሚያሳይ ሲሆን የኩላሊት ስራ ማቆምና ሞትን ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው። በሽታው ባልበሰሉ ምግቦች፣ በሳልና በማስነጠስ ወቅት እና ከታማሚ ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ፣ ባልታጠበ እጅ እና በመሳሰሉት ይተላለፋል።

የአለም ጤና ድርጅት የቫይረሱን ተጠቂነት ለመቀነስ እጅን በሳሙና መታጠብ፡ በሣልና በንጥሳት ጊዜ አፍንጫንና አፍን መፈን እና ከቤትና ከዱር እንሰሳት ጋር ያልተጠበቀ ግንኙነትን ማሰውገድ የቫይረሱን ተጠቂነት እንደሚቀንስ በድረ ገፁ አስፍሯል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here