ያገለገሉ ንብረቶችን በማስወገድ ከ32 ሚሊዮን ብር ተገኘ

0
560

የመንግሥት ንብረት ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት በስድትስት ወራት ውስጥ ያለገሉ ንብረቶች በማስወገድ ከ32 ሚሊዮን 699 ሺህ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ለአዲሰ ማለዳ አስታውቋል፡፡ ከተወገዱት ንብረቶች መካከልም ከሃያ መሥሪያ ቤቶች 65 ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከ28 ሚለየን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡

የ6 መሥሪያ ቤቶችን 580 ሎት ንብረት እና የአንድ መሥሪያ ቤት 14 ኮርማዎችን በሽያጭ በማስወገድ ደግሞ ከ2ሚሊዮን 636 ሺህ ብር በላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን የሁለት መሥሪያ ቤቶች 63,300 ኪሎ ግራም ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን በማስወገድ ከአንድ ሚሊዮን 462 ሺህ ብር በላይ ገቢ አግኝቷል፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት የ6 ተሽከርካሪዎችን ግዢ ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ውል በመፈጸም የተሽከርካሪዎችን በመግዛት ለተጠቃሚው መሥሪያ ቤቶች ተላልፏል፡፡

እንዲሁም ለኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የ400 ሺህ ሜትሪ ክቶን ስንዴ ግዥ ከ2ቢሊየን703 ብር እንዲሁም ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የ200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ በብር 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ተፈፅሟል፡፡ በድምሩም 3ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የግዢ ውል ለሶስት አሸናፊ ድርጅቶች የአሸናፊነት ደብዳቤ ተቋሙ ተሰጥቷል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here