ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ካሳ ያልተከፈለበት መሬት ለግጭት ምክኒያት እንደሆነ ገለፀ

0
466

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 250 ሄክታር መሬት በመኖሩ የተቋሙን ወሰን ማስከበር አለመቻሉን እና ይህም ለሰላማዊ የትምህርት ሂደት እንቅፋት እየሆነ መምጣቱን አስታወቀ።

መሬቱም ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመበት 1999 ጀምሮ የተጓተተና ካሳ ያልተከፈለበት 250 ሄክታር መሬት በመኖሩ ወሰኑን ማስከበር አለመቻሉንና ይህም ለሰላማዊ መማር ማስተማር ስራው እንደ ስጋት የሚታይ መሆኑን ገልጿል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ሲሆን ለመማር ማስተማር ስራው እንቅፋት የሚሆኑና ከዩኒቨርሲሰቲው አቅም በላይ በመሆናቸው የፌደራልና የክልል መንግስታትን ድጋፍ ይፈልጋሉ ያላቸውን ነጥቦች አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በተቋቋመበት ወቅት የነበረው አመራር የካሳ ክፍያውን ባለመጨረሱ በአሁኑ ስዓት ላለው የመማር ማስተማር ስራ እንቅፋት በመሆኑ በአፋጣኝ ሊፈታ እንደሚገባ አሳስቧል። የውሃ፣ የመብራትና የቋሚ አመራር ምደባ ጉዳዮች ለዩኒቨርሲቲው መማር ማስተማር ስራ መስረታዊ ቢሆኑም በአገልግሎቶቹ ላይ ከፍተኛ ጭግር በመኖሩ ችግሩ እንዲፈታ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው ለሚኖሩ አርበቶ አደር ማህበረሰቦችን ኑሮ መሰረት ያደረጉ በርካታ ጥናት እና ምርምሮችን በማከሄድላ የሚገኝ ሲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት የሚችል ሪፈራል ሆስፒታል በራሱ በጀት በማስገንባት ላይም ይገኛል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here