ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

0
771

 

ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ የካቲት 10/2012 ማካሄድ   ጀመረ።

በጉባዔውም  የክልሉ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችም ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ይፀድቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን

ጨፌው በመደበኛ ጉባዔው በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ እንደሚመክርም ተገልጿል።

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here