የአማራ ክልል የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኘሁ ተሻገር በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ደረጃ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን የሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮው በማኅበራዊ ገጹ አስታውቀ፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 10/2012 ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በአገኘሁ ተሻገር ቦታ ሲሳይ ዳምጤን የክልሉ ሠላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።



