የቻይና ኩባንያ በ1.5 ቢሊየን ብር ለትራንስፖርት ቢሮዎች ህንፃ ሊገነባ ነው

0
795

የቻይናው ዞንግያንግ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ኩባንያ ለአዲስ አበባ ትራንስፓርት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል ባለ 21 ወለል ህንፃ በ1ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ሊገነባ መሆኑ ታወቀ።

የቢሮው የኮሙዩኒኬሽን ቡድን መሪ አረጋዊ ማሩ ለአዲሰ ማለዳ እንዳስታወቁት ህንጻው የሚገነባው መገናኛ አካባቢ ከዘፍመሽ ፊት ለፊት በሚገኘው የቀድሞው የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ሲሆን ግንባታውን ለማጠናቀቅም ኹለት ዓመት እንደሚፈጅ አረጋዊ ገልጸዋል፡፡

የሚገነባው ህንጻ ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮና ለተጠሪ ተቋማት ዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ሲሆን ለተጠሪ ተቋማት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች እንደሚኖሩት ጠቅሰዋል፡፡

ህንጻው ከመሬት በታች ሶስት ወለሎች እና ከመሬት በላይ ደግሞ 21 ወለሎች ያሉት ሲሆን ግንባታው የትራንስፖርት ሙዚየም ማዕከላትን ያካትታል ተብሎ ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here