የጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ ፐሮጀክት ግንባታ 70 በመቶ መድረሱን ተከትሎ 6ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ለማምረት ዝግጁ ቢሆንም 235 ሚሊዮን ብር ብድር ባለማግኘቱ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ ዘገበ።
የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አንተነህ አሰጌ እንደተናገሩት ከሆነም ባንኮች ብድር እንዲሰጡን የጠየቅን ቢሆንም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
በአሁን ወቅት 13ሺሕ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ የተተከለ ቢሆንም ለምርትነት ዝግጁ የሆነው 2ሺህ ሄክታር ብቻ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የፋብሪካው ግንባታ በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው ሙሉ በሙለው ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በመጪው ግንቦት ወር የሙከራ ምርቱን ለመጀምር በዝግጅት ላይ መሆኑን አንተነህ ገልጸዋል።



