የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት 235 ሚሊዮን ብር ብድር ባለማግኘቱ ስራው እንደተስተጓጎለበት ገለጸ

0
687

 

የጣና በለስ ቁጥር አንድ የስኳር ፋብሪካ ፐሮጀክት ግንባታ 70 በመቶ መድረሱን ተከትሎ  6ሺህ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ ለማምረት ዝግጁ ቢሆንም 235 ሚሊዮን ብር ብድር ባለማግኘቱ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ ዘገበ።

የፕሮጀክቱ  ዋና ስራ አስኪያጅ አንተነህ አሰጌ እንደተናገሩት ከሆነም ባንኮች ብድር እንዲሰጡን የጠየቅን ቢሆንም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

በአሁን ወቅት 13ሺሕ ሄክታር የሸንኮራ አገዳ የተተከለ ቢሆንም ለምርትነት ዝግጁ የሆነው 2ሺህ ሄክታር ብቻ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የፋብሪካው ግንባታ በመጠናቀቅ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው ሙሉ በሙለው ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በመጪው ግንቦት ወር የሙከራ ምርቱን ለመጀምር በዝግጅት ላይ መሆኑን  አንተነህ ገልጸዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here