ኢትዮጵያ በብድር ጫና ከከፍተኛ ወደ መካከለኛ ስጋት ተሸጋገረች

0
514

 

ኢትዮጵያ ከውጭ አገራት የወሰደችው የብድር መጠን ከ27 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ አገሪቱ ከብድር ጫና ከከፍተኛ ስጋት ወደ መካከለኛ ስጋት መሸጋገሯን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።

ይህም የተረጋገጠው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና ዓለም ባንክ ጋር በጋራ ባከናወኑት የብድር ጫና ትንተና ላይ መሆኑን ያስታወሰው ሚኒስቴሩ ለዚህም እንደ ምክንያት ያነሳው የቻይና የንግድ አበዳሪዎች የዕዳ ክፍያ ጊዜ ሽግሽግ እንዲራዘም መደረጉን ነው።

ኢትዮጵያ በግማሽ ዓመቱ ከዓለም ባንክ እና ከሌሎች የገንዘብ ተቋማት 2ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ያገኘች ሲሆን በእርዳታ ደግሞ 13 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አግኝታለች።

ከቻይናና ከልማት አጋር መንግስታት ደግሞ 9ነጥብ3 ቢሊዮን ብር ብድር  ስታገኝ 13 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር እርዳታ ማግኘቷን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በ2012 ግማሽ ዓመት ውስጥ ከ39 ነጥብ ቢሊዮን ብር ብድርና እርዳታ ማግኘቷን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here