የውንብድና ወንጀል የፈፀሙ ሦስት ተከሳሾች የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

0
842

ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አካባቢ ከምሽቱ 4 ሰዓት የውንብድና ወንጀል የፈፀሙት ተከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው።

የወንጀሉ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ተከሳሾች ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) እና 671/2/ የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አካባቢ ከምሽቱ 4 ሰዓት ልዩ ቦታው ናዝራዊ ሆቴል አካባቢ ከሌሎች ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ያልታወቀ ሚኒባስ መኪና እያሽከረከሩ በመምጣት ሟች ኪሩቤል የተባለውን እና 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ታክሲ በመጠበቅ ላይ ሳሉ፣ “ቦሌ ቦሌ” በማለት በመጥራት ሟች እና ምስክር ወደ ታክሲ ውስጥ እንዲገቡ ካደረገ በኋላ ምስክሯ በመጠራጠር ሟችን እንውረድ በማለት ወራጅ ቢሉም 1ኛ ተከሳሽ ሟችን አንቆ ሲይዘው 3ኛ ተከሳሽ በቦክስ ደጋግሞ እንደመታው የአቃቤ ሕግ ምርመራ ያስረዳል።

በተጨማሪም የሟችን ሳምሰንግ ሞባይል የዋጋ ግምቱ 20 ሺሕ ብር፣ የምስክሯን አይ ፎር ሲክስ የዋጋ ግምቱ 16 ሺሕ 800 ብር እና አራት መቶ ብር ከወሰዱ በኋላ ሟችን እና ምስክሯን መንገድ ዳር ጥለዋቸው በመሄድ የወሰዱትን ሞባይል ሸጠው ተከፋፍለዋል። ሟች ኪሩቤል በደረሰበት የአንገት መታፈን ምክንያት ሕይወቱ ያለፈ በመሆኑ ተከሳሽች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ዐቃቤ ሕግ እንደ ክሱ አቀራረብ የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አጠናቅሮ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን፣ የክስ ዝርዝሩ በችሎት የተነበበላቸው ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምንም በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን በመስጠታቸው የምስክሮች ቃል ተሰምቷል። ተከሳሾች በተከሰሱበት ከባድ የውንብድና ወንጀል የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ችሎት መጋቢት 1 ቀን 2012 ክሱና ማስረጃውን ከሕግ ጋር አገናዝቦ ሦስቱንም ተከሳሾች እያንዳንዳቸውን በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 73 መጋቢት 19 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here