ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እና በህዝብ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኮማንድ ፖስት ስር እደማይተዳደር ተገለፀ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስተዳድረው በዋናነት የሚኒስተሮች ኮሚቴ እንደሆነም ተገልፀዋል፡፡ ይህም እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት ከዚህ በፊት በኢትዮጲያ ተጥሎ በነበረው በኢትዮጲያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ (ኮማንድ ፖስት) የሚለው ከዚህ ቀደም የአስተዳደር ስያሜ የፈጠረውን አሉታዊ ስሜት ለማስወገድ ታስቦ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአምስት ወራት ነው ተግራዊ እንደሚደረግም ይፋ ተደርጓል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ነገር ግን የመብት እገዳዎቸ እና እርምጀዎችን ዝርዝር ሁኔታ በየጊዜው በሚኒስተሮች ምክር ቤት ወይንም የሚኒስተሮች ምክር ቤት ለዚሁ አላማ በሚያቋቁመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እየተወሰነ እንደሚሄድ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አዳነች አቤቤ መጋቢት 30/6/2012 በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል፡፡
በተያያዠም የትግራይ ክልል ምክር ቤት 1/7/2012 በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽንን ለመከላከል ቀደ፣ም ሲል ደንግጎት የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ሶስት ወራት አራዝሟል፡፡
ምክር ቤቱ የአዋጁን አስፈላጊነት እና ይዘት ከመረመረ በኋላ ቀደም ሲል ወስኖት ከነበረው ከመጋቢት 17/2012 ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት እንዲቀጥል መወሰኑ ተገልፀዋል፡፡
ምክር ቤቱ አዋጁን ያራዘመበት ምክንያትም የቫይረሱ ስርጭት በተለያዩ አገራት ፍጥነቱን ጨምሮ በአስጊ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተከትሎም እንደሆነ ታውቋል፡፡
ቅጽ 2 ቁጥር 75 ሚያዝያ 3 2012



