ዩኒሴፍ እና የእንግሊዝ መንግስት በጋራ የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

0
525

በእንግሊዝ መንግስት እና በተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በጋራ ባደረጉት ትብብር የ1ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶችን ለኢትዮጵያ አበርክተዋል። የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የዩኒሴፍ ተወካይ በኢትዬጵያ አደል ኮድር በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መጋዘን በመገኘት ርክክብ አድርገዋል፡፡
ድጋፍ የተደረጉት የህክምና ግብዓቶች N95 የፊት እና የሰውነት መሸፈኛ ጭምበልን ጨምሮ ለኮሮና በሽታ ለመከላከል የሚስችሉ ግብዓቶች መሆናቸው በርክክቡ ወቅት ተገልጾል፡፡ ዶክተር ሊያ በበኩላቸው በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ድጋፍ መደረጉ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ያለውን ዝግጁነትና ምላሽ ሰጭነት የሚረዳ እና ጤና ባለሙያዎች ያለምንም ስጋት ለማከም እንዲችሉ እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸው የተደረገልን ድጋፍ እጅግ አድርገን እናመስግናለን ብለዋል ገልጸዋል፡፡ የዩኒሴፍ ተወካይ በኢትዮጵያ የሆኑት አደል ኮድር በበኩላቸው ይህ እገዛ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጸው ድጋፉ የሚቀጥል መሆኑን በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመግታት የቁሳቁስ እና ገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላት እንደሚገኝ የሚታወቅ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 77 ሚያዝያ 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here