በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 1 ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰብ ኢትዮጵያዊት ሴት ሲሆኑ ነዋሪነታቸው በባህ ዳር ከተማ ሆኖ በቫረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 131 ያደረሰው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 67 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ህክምናና እንክብካቤ እየተደረገላቸው ያለ ሲሆን 59 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል፡፡




