የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባው በቀደመው የ5ኛ አመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ እና 2ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ የሰፈሩ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ በሙሉ ድምጽ ያፀደቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ገምግሞም አፅድቋል።
በመደበኛ ስብሰባውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ወይዘሪት ብርትኳን ሚደቅሳ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ማብራሪያና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል ባቀረቡትም የውሳኔ ሀሳብ በቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የመራጮች ምዝገባ የሚጀምረው ከሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ቢሆንም በሀገሪቱ ውስጥ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሣቢያ በርካታ ህዝብዊ እንቅሰቃሴዎች በመገደባቸው የምርጫው ጊዜው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ እንዳልተቻለ ገልጸዋል።
የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው የምርጫ ቦርድ ከዚህ በፊት ምርጫውን ለማካሄድ የሚችልበትን የጊዜ ሰሌዳ በግልጽ ለህዝብ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ወረርሽኙ በአለምና በአገራችን በመከሰቱ መንግስት ቅድሚያ ለሕዝብና ለሀገር በሚል በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ሲለሆነም ቦርዱም ከዚህ ጊዜ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል መግለጹን ተገቢነው ብለዋል፡፡
በቀረበው አጀንዳ ላይ የምክር አባላት የተለያዩ አስተያየት እየሰጡ ሲሆን ቦርዱ የምርጫ ጊዜውን ማራዘሙ ተገቢ ቢሆንም በአገሪቱ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስን ወረርሽኝ ነው ለማለት ይቻላል ወይ? የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት ቀርቧል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው የምክር ቤት አባላት በሽታው ወረርሽኝ እንደሆነና መንግስት ወረርሽን መሆኑን አምኖ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከማወጁ በላይ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ መዝጋቱንና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎችን መገደቡን ጠቁመው ቦርዱ ያቀረበውን ውሳኔ ተቀብሎ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን አግባብ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አደራሽ እያካሄደ የሚገኘው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ሀሳቦች ላይ የተሰጡ ውሳኔዎችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ተጠብቆ የነበረ ሲሆን በዚህም መሰረት
የምክር ቤቱ አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሴ ጫፎ ቦርዱ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ መሆኑን ጠቁመው ቦርዱ በራሱ የስልጣን ወሰን ውሳኔ መስጠቱን የመጨረሻውሳኔም የምክር ቤቱ መሆኑን ጠቁመው ለድምጽ አቅርበዋል፡፡ ውሳኔውንም ምክር ቤቱ በአንድ ተቋሞና በ18 ድምጸ ታዕቅቦ ወስኗል፡፡
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርብ ለህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴውሳኔ ቁጥር 8/2012 ሆኖ በ3 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል፡፡
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በሳዑዲ የልማት ፈንድ መካከል ለሁለተኛው አገር አቀፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ሳኒቴሽንና ሃይጂን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ረቂቅ ወደ ሁለታኛ ንባብ እንድሸጋገር አዋጅ ቁጥር 1192/2012 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁም ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኮሪያ ኤክስፖርት- ኢምፖርት ባንክ መካከል ለአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲ የልዕቀት ማዕከል መመስረቻ ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሁለታኛ ንባብ ተሸጋግሮ እንድ ጸድቅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቀብል ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1194/2012 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡
እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በሳዑዲ የልማት ፈንድ መካከል ለደብረማርቆስ-ሞጣ የመንገድ ስራ ማሻሻያና ማሳደጊያ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ ወደ ሁለታኛ ንባብ ተሸጋግሮ እንዲጸድቅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቀብል ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1195/2012 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል ለቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሁለታኛ ንባብ ተሸጋግሮ እንድ ጸድቅ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በመቀብል ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1196/2012 ሆኖ በሙሉ ድምፅ ጸድቋል፡፡
ምክር ቤቱ የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽንን ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተወያይቶ ለሰው ሃብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እየታ የወሳኔ ሃሳብ ቁጥር 36/2012 ሆኖ በሙሉ ድምጽ መርቶታል፡፡







