በቀደመው ችሎት ፍርድ ቤቱን በተከሳሾቹ ላይ በተወሰኑ የክስ መዝገቦች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያስተላለፈው ፍርድ ቤቱ የቅጣት አስተያየት ለማዳመጥ ለዛሬ ሚያዚያ 28 ቀን 2012 ቀጠሮ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡
በዛሬው እለትም ችሎቱ የአቃቤ ሕግና የተከሳሾችን የቅጣት አስተያየት ያዳመጠ ሲሆን ተከሳሾቹ የጤና እክል ያላባቸው መሆኑንና አገሪቱን ለረጅም ጊዜ ማገልገላቸው እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው በማቅላያነት እንዲያዝላቸው ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡
በዚህም መሰረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አስተያዬቱን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠትም ለሚያዝያ 30 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡



