በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በ17 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

0
647

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 382 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ17 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ በአንድ ቀን የተመዘገበ ከፍተኛ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ነው፡፡

በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት ሰዎች ውስጥ 15 ወንዶች ሲሆኑ ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ አስራ ሦስቱ ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 30 ዓመት ያሉ ናቸው፤ ቀሪዎቹ ደግሞ እስከ 65 ዓመት ያሉ ጎልማሶች እንደሆኑ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት 13 ከጂቡቲና ሶማልያ ወደ ኢትዮጵያ የገቡና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው፤ ሁለቱ የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበራቸው ሴቶች ናቸው፤ አንደኛው በሙያው ለቫይረሱ ተጋላጭ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን ቀሪው አንድ ሰው ደግሞ የጉዞ ታሪክ የሌለውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ ነው፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት ሁለት ተጨማሪ ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውም ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለ26 ሺህ 517 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎ በ162 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱ ተረጋግጧል፤ ከእነዚህ ውስጥ 93 አገግመዋል፤ 63 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ሕክምና ክትትል ላይ ናቸው።

የቫይረሱን ስርጭት ከዚህ የከፋ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄዎች አዘውትሮ በመተግበር እንዳይዘነጋም የጤና ሚኒስቴርና  የእትዮጵያ ህብረተሰብ ሳይንስ ኢኒስቲትዮት በጥብቅ አሳስበዋል፡፡

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here