በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስን የመከላከል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው ተገለፀ

0
599

በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተሰራ የሚገኘውን ስራና በሂደቱም ላይ እያጋጠሙ የሚገኙ ተግዳሮቶችን የሚገመግም መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

እንደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ በግምገማ መድረኩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸው ታውቋል  ።

በመድረኩ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመለየት ስራው በሰፊው የተሰራ ቢሆንም ከድንበር ተደብቀው ገብተው ራሳቸውን ለይተው የማያቆዩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱና በተለይም ከኬንያና ሶማሊያ በድንበር አቋርጠው ከገቡ በኋላ ህዝብ ጋር የሚቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ እንደዋና ስጋት ሊታይ እንደሚገባው ተገልጿል።

የመመርመሪያ ላቦራቶሪና የለይቶ ማቆያ ስፍራ ዝግጅት በጥሩ ደረጃ ላይ ያለ ቢሆንም የህክምና ባለሙያዎች ራስን መጠበቂያ ቁሳቁስ እጥረት እንዳይኖር መሰራት እንዳለበት ተጠቁሟል።

ምርትን መደበቅ፣ አላግባብ ዋጋ መጨመር በሰፊው የተስተዋለ ችግር መሆኑም በግምገማ መድረኩ የተጠቆመ ሲሆን በትራንስፖርት በኩል በተለይ የሌሊት ጉዞን ለማስቀረት ሰፊ ስራ መሰራቱ ተገልፆል።

የበጎ አድራጎት ስራዎች ለመከላከል ስራው አጋዥ ሆነው እንደቀጠሉና በርካታ ባለሃብቶች ድጋፍ ማድረጋቸውም ታውቋል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የመከላከል ስራው በክልሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም መጠየቁም ከ ኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here