የታላቁን ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በመጪው ሐምሌ ወር የመጀመር እቅዷን ተግባራዊ እንደምታደርግ ኢትዮጵያ አስታወቀች

0
790

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩትና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተሳተፉበት የህዳሴ ግድብ የቴክኒክ ኮሚቴ በውሃ መስኖ ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አማካኝነት የግድቡን ዝርዝር የስራ ሂደት የተመለከተ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተከሄደበት ይገኛል።

እንደ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘገባ በሪፖርቱ የሲቪል ምህንድስና ስራው 87 በመቶ ጥቅል የግንባታ ሂደቱ ደግሞ 73 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት በሐምሌ ወር የመጀመርያውን የውሃ ሙሌት ስራ ለማስጀመር የሚቻልበት የግንባታ ደረጃ ላይ በመደረሱ ይህም ተግባራዊ እንደሚደረግ ዶ/ር አንጂነር ስለሺ ተናግረዋል።

የውሃ ሙሌቱ እንዳይጀመር ግብፅ ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክር ቤት ቅሬታ ማስገባቷን በተመለከተም ኢትዮጵያ ተገቢውን የምላሽ ሰነድ ማዘጋጀቷንም አስታውቀዋል።

የታችኛው ተፋሰሰ ሀገራትን ያካተተው የዋሽንግተኑ መድረክ ለውይይት ክፍት ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ ወደ መድረኩ እንደማትመለስም በሪፖርቱ ተገልጿል።

የመጀመርያው ሙሌትን ማስጀመርን በተመለከተ ከዚህ ቀደም በግብፅም ሆነ በሱዳን በኩል ስምምነት የነበር ቢሆንም አሁን ግን የሙሌት አተጋባሩን የሚገልፀውን ቴክኒካል ሰነድ እንዲላክላቸውና እንዲመለከቱት ሲጠየቁ በሁለቱም በኩል ፍቃደኝነት አለመኖሩም የተጠቆመ ሲሆን ኢትዮጵያ አሁንም የሶስትዮሽ ድርድሩ ቀድሞ በተቀመጡ መርሆች ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔን ሊሰጥ በሚችል መልኩ እንዲቀጥል ቢደረግ ፍቃዷ መሆኑም ተገልጿል።

ቀድሞም የምታራምደውን የጋራ ተጠቃሚነት መርህን እንደምትቀጥልም እንዲሁ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩት በዚህ ውይይት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መሳተፋቸውን ከ ኢ ቢ ሲ ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here