10ቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር ለዓለም ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያሰማሩ አገራት

0
770

ምንጭ፡- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (2020)

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል የሆኑ አንድ መቶ ዘጠና ሦስት አገራት ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወታደሮቻቸውን ያሰማራሉ። ከዚሀም ውስጥ ለዓለም ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ብዙ ወታደሮቻቸውን በማሰማራት በአስርቱ ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት፤ ኢትዮጵያ 6 ሺሕ 386 ወታደሮችን በማሰማራት አንደኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ፤ ባንግላዲሽ እና ሩዋንዳ ኹለተኛ እና ሦስተኛ ላይ ተቀምጠዋል።
ሕንድ፣ ፓኪስታን እና ቻይና ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ጋና እና ታንዛኒያ ከሰባት እስከ ዘጠኝ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በመጨረሻም ግብፅ 2 ሺሕ 181 ወታደሮችን በማሰማራት አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በተያያዘም በአሜሪካ ደግሞ ለሰላ አስከባሪ ወታደሮች ከሚበጀተው ዓመታዊ በጀት 27.8 በመቶውን በመደጎም ቀዳሚ ስትሆን፣ ቻይና 15.21 እንዲሁም ጃፓን 8.56 በመቶ ድጎማ በማድረግ በገንዘብ እንደሚያግዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

ቅጽ 2 ቁጥር 82 ግንቦት 22 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here