በኢትዮጵያ ተጨማሪ 87 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የተጨማሪ 2 ሰዎች ህይወትም በበሽታው ምክንያት አልፏል

0
414

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 3,932የላቦራቶሪ ምርመራ 87 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውና የተጨማሪ 2 ሰዎች ህይወት እንዳለፈ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

በዚህም እስካሁን በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል።

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 59 ወንድና 28 ሴቶች ሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እና እድሜያቸው ከ 10 እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 6 ኦሮሚያ ክልል፣ 7 ሰው ከአማራ ክልል 1 ከሀራሪ ክልል እንዲሁም 4 ሰዎች ከሶማሌ ክልል መሆናቸው ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ፡-

28 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣

18 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው

እንዲሁም 41 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም በዛሬው እለት የ30 ዓመት ዕድሜ እና የ56 አመት እድሜ ያላቸው የ2 ኢትዮጵያዊያን ሕይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርን 14 አድርሶታል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት ተጨማሪ 14 ሰዎች ( 6 ሰዎች ከኦሮሚያ እንዲሁም 8 ሰዎች ከሶማሊያ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 23 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ባሁኑ ሰአት 8 ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 1097 ናቸው።

እስካሁን በኢትዮጵያ አጠቃላይ 116,309 የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑንም ከሚኒስትሯ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here