የአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል ጀመረ

0
1180

የአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶች በማማላት የኮቪድ-19 ህክምና ማዕከል ሕሙማንን መቀበል መጀመሩ ተገለፀ፡፡

የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን ለኢዜአ እንዳሉት ባለፉት ሁለት ወራት ማዕከሉን የማደራጀት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን የገለፁ ሲሆን 1 ሺህ 200 ታማሚዎችን መያዝ እንዲችል ተደርጎ ተደራጅቷል ብለዋል።

በተጨማሪም ማዕከሉ 40 የጽኑ ሕሙማን መኝታዎችና 1 ሺህ ጽኑ ያልሆኑ ሕሙማን ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል፡፡ ጎን ለጎንም የላቦራቶሪ፣ የመድሃኒት ቤት፣ የጤና ባለሙያዎች ልብስ መቀየሪያ፣ መታጠቢያዎችና ሌሎች ክፍሎችም ተዘጋጅተዋል።

በማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ ሕሙማንና ለጤና ባለሙያዎች አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውንም ጠቅሰዋል።

በተጓዳኝም ከማዕከሉ የጥበቃ ሠራተኞች ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ነርሶችና ዶክተሮች ሥልጠናም ተሰጥቷል።

በዚህ መሰረት የማዕከሉ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ ሐሙማንን መቀበል መጀመሩን ነው ዶክተር እስማኤል ለኢዜአ ተናግረዋል።

በማዕከሉ ሕሙማን አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ፤ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ሠራተኞችም ለቫይረሱ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ትኩረት መሰጠቱንም አክለው ገልፀዋል።

በተለይም የአየር ሥርዓት ፍሰቱን ለማስተካከል የሚረዱ መሣሪያዎች መገጠማቸው ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ከማዕከሉ የሚወገዱ ፍሳሾች ለብቻ እንደሚወገዱና ደረቅ ቆሻሻዎችም በዘመናዊ መሣሪያ በመታገዝ የሚወገዱ መሆኑንም ዶክተር እስማኤል ተናግረዋል።

በማኅበረሰቡ ዘንድ የኮቪድ-19 ማዕከላትን የመፍራት ሁኔታዎች መኖሩን የጠቆሙት ዶክተር እስማኤል ይህ አመለካከት ሊቀየር እንደሚገባም አሳስበዋል።

በዚህ ረገድ በማዕከሉ ለሕሙማን የጤና ትምህርቶችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ጭምር ለመሥጠት ዝግጅት መደረጉን መገለፃቸውን ከኢ.ዜ.አ ያገኘነው ዘገባ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here