የአደባባይ ላይ ስብከቶች ቁጥጥር ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ

0
909

በሌላ ኃይማኖት ላይ ዘለፋ እና ተንኳሽ የሆኑ የአደባባይ ላይ ስብከቶች የሚመለከተው አካል ቁጥጥር ሊያደርግባቸው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ

የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰኔ 1/2012 ለፌደራል ፖሊስ በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም የበርካታ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና የዲፕሎማቶች መገኛ በሆነችው አዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የሃይማኖት ሰባኪዎች ከቤተ እምነቶቻቸው ቅጥር ግቢ ውጪ በመውጣት በአደባባይ ላይ የራሳቸው ወገን ያልሆኑ የዕምነት ተከታዮችን በሚተነኩስ መልኩ ሃይማኖታዊ ትምህርቶች እየሰጡ እንደሚገኙ እና አንዳንድ ቦታዎችም ይህንኑ ትምህርት ከፍተኛ ድምፅ በሚያወጡ ድምፅ መሳሪያዎቸ ጭምር የሚታገዝ ሲሆን ይህም ለሌሎች ተግባራት እና አገልግሎት ከሚለቀቁት ድምጾች ላይ ተጨምሮ ህብረተሰቡ ለተሉያየ የድምፅ መበከል እና ስነ- ልቦና ጉዳት እየደረሰባቸው በመሆኑ እንደሆነ ታሳቢ በማድረግ መሆን በደብዳቤው አስታውቋል፡፡

ከዛ በተጨማሪም ደግሞ በ ኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 44 (1) ላይ ማንኛውም ሰው በንፁህ እና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት ያላቸው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ይህንንም የህገ መንግስቱን ድንጋጌዎችን ተፈፃሚ ለማድረግ የድምፅ መጠንን ለመወሰን መመርያም ስላለ በዛ መሰረት ተፈፃሚ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ አይንተ ህገ መንግስታዊ መብት ህብረተሰቡ እለው በተለያዩ አካባቢዎች ቡና ቤቶች መጠጥ ቤቶች ፣ጋራጅ ቤቶች ፣ የብረታ ብረት ብየዳዎች ፣ ጎዳና ላይ ንግድ ማስታወቂዎች እና ቅስቀሳዎች የሚወጣው ድምጽ መጠን በህግ ከተቀመጠው በላይ እንደሆነ እና ከቅርብ ግዜ ወዲ ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትና በአደባባዮች የሚለቀቁት ድምጾች በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን የጆሮ ጤንነት እየጎዱ እንደሆነ በተለያየ ጊዜዎች በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለኢትዮጲያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አቤቱታዎች እንደሚደርሱ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ ሃይማኖት ተቋማት አስተማሪዎች እና ሰባኪያን ከፍተኛ ድምፅ በሚለቁ የድምጽ መሳሪያዎችን በመጠቀም ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የጎዳና ላይ ስብከት እያደረጉ ሲሆን አልፎ አልፎም በእምነት ወደ ማይመስሏቸው ቤተ እምነቶች ስፍራ በመጠጋት ያስተምራሉ፡፡ ይሁን እነጂ እንደ ኢትዮጲያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለጻ ከሆነ ጎዳ ላይ ትምህርት ይዘት አስፈላጊ ሲሆን ሁሉም አማኞች በመንፈሳዊ ህይወታቸው እንዲጠነክሩ ስብከቱ ቤ አጥቢ ቤተ እምነቶች ተጠናክሮ ቢሰጥ ተቋሙም የሚደግፈው ነገር ነው ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን እየቀረቡ ያሉት የአደባባይ እና የጎዳና ላይ ስብከቶች የራስ እምነትን ከመግለፅ ባለፈ የሌሎችን እምነት እና አስተምሮ መተንኮስ አዝማሚያ የሚታይባቸው እና ከገምቢነታቸው ይልቅ አፍራሽነታቸው እየጎላ እንዲመጣና ቅድሚያ ካልታረመ በተለያየ ሃይማኖት ተከታዮች እና አማኞች መካከል የግጭት መንስዔ መሆን እድሉ ሰፊ ሊሆን እንደሚችል እንዳሰጋው የኢትዮጲያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገልጿል፡፡

የጉባዔው ሊቀመንበር ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለአዲስ ማለዳ እንደሚሉት በዚህ ማስጠንቀቂያ ላይ የተለየ የሃይማኖት ተቋም የለም ፤ ነገር ግን እንዲህ እንዲደረግ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት ከሃይማኖቶቹ ከሁሉም ቤተ እምነት ከእነርሱ እውቅና ውጪ የሚንቀሳቀሱ አሉ ያሉ ሲሆን፤ ‹‹ የኦርቶዶክሱም እንደ ባህታዊ ነን የሚሉ››፣ ‹‹በፕሮቴስታንትም ሊሆን ይችላል ነብይ ነን የሚሉ››፣ ‹‹በእስልምናም ሊሆን ይችላል ዱአ እናረጋለን የሚሉ›› ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ገልጸዋል።
ድምጽ ማጉያዎችን ተከራይተው ለረጅም ጊዜ ሌሎችን ሃይማኖት በመግፋት ለሌሎች ቤተ እምነት በር ድረስ በመጠጋት ወደ ግጭት የሚዳርጉ ተግባራት እየተፈጠሩ መሆናቸውንም ለአዲስ ማለዳ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

‹‹ እኛ ከንሰሃ መግባቱ እና ከትምህርቱ ጋር አደለም ችግራችን ግጭት በሚያስነሳ ጉዳይ ግን የሚደረጉ ትንኮሳዎች ስለሆኑ የሚተላለፉት መልክቶች ይዘቶቻቸው ላይ እንደ ተቋም ይሄን መቆጣጠር እንዳይከሰቱ ማድረግ የኛ ሃላፊነት ነው፡፡ ይሄም ያስፈለገው በዚህ ምክያት ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ለመቆጣጠር ከመሮጥ ቀድሞ መጠንቀቅ ያሥፈልጋል›› ሲሉ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

ከቤተ እምነት ጊቢ ውጪ የሚደረገውን መቆጣጠር ያለበት ህግ አስከባሪ እንደመሆኑ መጠን እኛ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፅፈናል፤ ከኛ የሚጠበቀውን አድርገናል ያሉት ቀሲስ ታጋይ ቀጣዩ የሕግ አስከባሪዎች ስራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 84 ሠኔ 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here