ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በሚደርስባቸው ከፍተኛ መገለል ሥራቸውን እየለቀቁ ነው

0
887

የድንበር ተሻጋሪ መኪኖች አሽከርካሪዎች በጉዟቸው ወቅት በሚያቋርጧቸው ኢትዮጵያ ከተሞች እና በኑሯቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ መገለል እየደረሰባቸው በመሆኑ ሥራ ለመልቀቅ መገደዳቸውን አስታወቁ።

ለአዲስ ማለዳ ማብራሪያቸውን የሰጡት የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ማኅበር ዋና ስራ አስኪያጅ ክብረት አለማየሁ እንደገለጹት በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች በጉዟቸው ወቅት ከዚህ ቀደም ተሸከርካሪዎችን በማቆም ዕረፍት ያደርጉባቸው በነበሩ ከተሞች እንዳያርፉ በነዋሪዎች መገለል እንደደረሰባቸው እና በጫካ ውስጥ አቁመው ሰው በሌለባቸው አካባቢዎች እንዲያርፉ እንደሚደረጉ ጠቁመዋል።

እንደ ክብረት ገለጻ ይህንም ተከትሎ በርካታ አሽርካሪዎች በጉዟቸው ወቅት ምግብ ለማግኘት እንኳን እንደተቸገሩ ለማወቅ ተችሏል። ከዚህም በተጨማሪ የከፋው ነገር ደግሞ አሽከርካሪዎች በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች በሚገኘው ቋሚ መኖሪያቸው እንዲለቁ እየተደረጉ መሆኑንም አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።
የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር እንደሚለው ከሆነ በኢትዮጲያ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነው ወጪ እና ገቢ ንግድ ( ማዳበርያን ጨምሮ) እንቅስቃሴ የሚደረግበት ዋነኛው አውታር ቢሆንም ነገር ግን አሁን ላይ በኅብረተሰቡ ዘንድ ግን በአሽከርካሪዎች ላይ የማግለል እና ስራውን እንዲቆም የሚያደርግ ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የፌደራል ትራንስፖርት ባለ ስልጣንን ጨምሮ በመንግስት ባለ ድርሻ አካላት የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆኑን ታዝበናል ብሏል።
ቢሆንም በድምበር ተሸጋሪ ሱፌሮች ላይ መገለሉ እንዳለ ሆኖ ከሚደርሱባቸው ተፅዕኖዎች መካከል ተሸከርካሪ በሚያሳርፉበት ቦታዎች ላይ እንዳያቆሙ እየተደረጉ ሲሆን የማይሆን የህግ ከለላ በሌለበት ቦታ ሄደው ሲያሳርፉ ለዝርፊያ እና ለግድያ እየተዳረጉ መሆኑንም ማኅበሩ ለአዲስ ማለዳ ተናግሯል። የፀጥታ አካላት ይሄንን ትብብር ሊደርጉላቸው ይገባል ያለው ማህበሩ። በዋነኛነት የሚመገቡት ምግብ እንኳን እናዳያገኙ እና ሲገኝም ደግሞ እንዳይጠቀሙ የማድረግ እንቅስቃሴዎችንም ኮንኗል።

ከዛም በተጨማሪ የምድር ሚዛን አገልግሎት እንዳያገኙ እና የያዙትን እቃ ምን ያህል እንደሆነ ለማስመዘን ሲሉ እንዳይጠቀሙ እየተደረገ ነው ሲሉ ክብረት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በዚህም ምክንት ይላሉ የማህበሩ ሃላፊ ከጊዜ ወደ ጊዜ መስራት አልቻልንም በማለት የተሸርካሪዎችን ቁልፍ የሚስረክቡ አሽከርካሪዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን አስታቀዋል። ከዚህም ቀደም በቂ የሚባሉ የድንበር ተሻጋሪ ሾፌሮች የሉንም ነበር ነገር ግን አሁን ደግሞ በለጸ እጥረት እያጋጠመን ነው ብለዋል።
አጠቃላይ ያሉት የድምበር ተሸጋሪ ሾፌሮች ከ250 በላይ ሲሆኑ የማኅበሩ አባላቶቹ ደግሞ 60 ናቸው። ጅቡቲ ላይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እጥረት እለ የተሸከርካሪ( ሰሆፌሮቹም ፈቃደኛ አይደሉም ) ቁጥራቸው እየተለዋወጠ በመሆኑ ምን ያህል እንደሆነ) ባይታወቅም ነገር ግን በዚህ መክንት ቁጥራቸው የማይናቅ አሽከርካሪዎች ስራቸውን ትተዋል።

እንደ መሃበሩ ዋና ሃላፊ ገለጻ የህብረተሰቡ ካለ ቅጥ ማግለል እና ተፅ እኖው መበርታቱ ምክንት ‹‹ ሪፖርቱ አዘጋገብ ሂደት ነው›› ጤና ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን እለታዊ ሪፖረት ሲያወጣ ‹‹ አሽከርካሪዎች ብቻ ነው በስራ ዘርፋቸው ይፋ ሚሆነው ›› ለዚህም ተለይተው እንዲገለሉ እያደረገ ነው ብለዋል። መንግስት ሃላፊነት ወስዶ እዚህ ላይ ማሻሻያ ሊደርግ ይገባል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የፌደራል የትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይግዛው ዳኘው ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ ችግሩ ይሄን ያህል የተጋነነ አይደለም ችግሩ የተስተዋለው የተወሰኑ ሹፌሮች ላይ እንጂ ሁሉም ላይ አይደለም ለነሱም መፍትሄ ለመስጠት የፌደራል ትራንስፖርት ባለ ስልጣን እየሰራ ነው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

‹‹ እነሱ ቢያቆሙ ማዳበርያ ይቆማል›› እነሱ ቢያቆሙ የተለያዩ የአገሪቱ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ይመጣል ለዚህም ባለ ስልጣን መስርያ ቤቱ የራሱን ሃላፊነት ኬሚካል እርጭትን ጨምሮ በየ ኬላው ላይ የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎት የሚገኙበነት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ማድረግ ስራ እሰራን ነው ብለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 84 ሠኔ 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here