አብነት ገብረመስቀል የሚድሮክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል

0
902

ለረጅም አመታት ሚድሮክ ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸወን መልቀቃቸውን ተከትሎ በምክትላቸው ሲመራ የነበረው ሚድሮክ ኢትዮጵያን እንዲያስተዳድሩ አብነት ገብረ መስቀል ተሹመዋል፡፡

አብነት ገብረመስቀል በሚድሮክ ኢትዮጵያ ስር የሚንቀሳቀሱትን በኮንስክትራክሽን፣ በሆቴሎች እና በሪል ስቴት ዘርፍ ያሉትን ኩባንያዎች በሙሉ እንዲመሩ መመደባቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ በተጫማሪም አቶ ጀማል አህመድን በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ደረጃ በማንፋክቸርንግ፣ በማዕድን፣ በንግድ፣ በግብርና እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ያሉትን ኩባንያዎች እንዲመሩ መሾማቸውም ታውቋል፡፡

የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉት ዶክተር አረጋ ይርዳው ከሁለት ወር በፊት በፍቃዳቸው ከሃላፊነት መነሳታቸው የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here