የሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር አዲስ አበባ ገብተዋል።
ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገዱ አንዳርጋቸውና በጀነራል አደም መሐመድ አቀባበል ተደርጎለቸዋል።
ሌተናል ጀነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በቆይታቸው ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነትና በወቅተዊ ጉዳይ ዙሪያ እንደሚመክሩም ኢቢሲ ዘግቧል፡፡




