ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ 2 ሰዎች ህይወትም አልፏል

0
957

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ 5,274 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 129 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው እንዲሁም ተጨማሪ 2 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቀዋል።

ይህም በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,759 አድርሶታል።

እንደ ጤና ሚኒስቴር መግለጫ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 79 ወንድና 50 ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ 1 ዓመት እስከ 70 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡

በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ቫይረሱ በምርመራ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠው ሰዎች ውስጥ 85 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣

11 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣

10 ሰዎች ከሶማሌ ክልል፣

7 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣

6 ሰዎች ከአማራ ክልል፣

5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣

4 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም 1 ሰው ከአፋር ክልል መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በቫይረሱ ምክንያት የተጨማሪ 2 (የ60 ዓመት ወንድ የድሬዳዋ ነዋሪ በህክምና ማእከል በህክምና ላይ የነበረ)፣ (የ30 አመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማእከል በህክምና ላይ የነበረ) ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 63 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት ተጨማሪ 111 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን 849 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ቫይረሱ በሀገራችን እንደተገኘ ገተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በአጠቃላይ 197,361 የላብራቶሪ ምርመራዎች ተካሂደዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here