አቶ ኢብራሒም ዑስማን አቶ አደን ፋራህን በመተካት የሶማሌ ክልል ምክትል ርእስ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

0
853
አቶ ኢብራሒም ዑስማን አቶ አደን ፋራህን በመተካት የሶማሌ ክልል ምክትል ርእስ መስተዳድር ሆነው ሲሾሙ፤ መሎው ኢብራሒም አብዲ (ማንዴላ) ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

በሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዑመር የሚመራ የብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ ባካሔደው ሰብሰባ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ሁለት አዳዲስ ሹመቶችን አፅድቀዋል።

በዚህም ስብሰባው በቅርቡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙትን አቶ አደን ፋራህ ቦታ በመተካት አቶ ኢብራሒም ዑስማን የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አድርጎ መሾሙ ታውቋል።

እንዲሁም አቶ መሎው ኢብራሒም አብዲ (ማንዴላ) ደግሞ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

ይህም ሹመት በቀጣይ ለሶማሌ ክልል ምክር ቤት እንደሚቀርብ አብዶ ሂሎው ሐሰን ከሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን መዘገቡን ከኢቢሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here