ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

0
768

ከሰኔ 6 እስከ 10/12 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ብቻ ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ተሽከርካሪዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማና መለዋወጫ (ስፔር ፓርት)፣ የምግብ ዘይት፣ ጫት፣ ሃሺሽ እና ልዩ ልዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡

እንዲሁም በቦሌ፣ በሞጆ እና በአንዳንድ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ በተደረገው ከፍተኛ ቁጥጥር ብዛት ያላቸው የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎች ተለይተው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረገ ሲሆን 120,000 ሀሰተኛ ዶላርም በሞያሌ ቅርንጫፍ መያዙንም ሚንስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

የቁጥጥር ስራው በጣም አድካሚ ቢሆንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቀንና ሌሊት ህዝባቸውንና ሀገራቸውን በብዙ መስዋዕትነት ውስጥ ሆነው እያገለገሉ ያሉ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች፣ ሠራተኞች እና የፀረ-ኮንትሮባንድ አካላት እንዲሁም ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በየመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ ኮንትሮባንዲስቶችን በማጋለጥና ህገ-ወጥ ዕቃዎችን በመቆጣጠር ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here