ኢትዮጵያ ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት ለመጠቀም ወሰነች።
የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት “ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡”
የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን አነስተኛ መጠን ያለው ዴክሳሜታዞን እንደ ድኝገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል” ብለዋል።
ህክምናውን አስመልክቶ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ እንደሚወጣም ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።



