”የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ምቹ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ እንዲቻል በማቀድ በተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ አማካኝነት ዋና ዋና የሪፎርም ስራዎችን ማካሄድ ተችሏል” -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

0
1087

የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢ ምቹ፣ ተወዳዳሪና ተመራጭ ለማድረግ እንዲቻል በማቀድ በተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ አማካኝነት ዋና ዋና የሪፎርም ስራዎችን ማካሄድ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ የፌስቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ቁልፍ የሕግና የአስተዳደራዊ ለውጦችን ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን ባለፈው ዓመት ከተደረጉት የሕግ ማሻሻያዎች የሚከተሉት አበይት ስራዎች እንደሚገኙበትን ተናግረዋል፡፡

-የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ማሻሻያ አዋጅ 1150-2011 እና ደንብ 461-2012

– በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሰረት የዋስትና መብት አዋጅ 1147/2011 እና ማስፈፀሚያ መመሪያ

– የብድር መረጃ ቋት ማቋቋሚያ መመሪያ ቁጥር CRB-01-2012

– የተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 11572011

– የኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር 1180-2012

– የኢንቨስትመንት አዋጅ ለማስፈፀም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ

– ኤሌክትሮኒክ ንግድና ግብይት አዋጅ

– አዲስ የንግድ ሕግ (በሚኒስቴሮች ም/ቤት የጸደቀ)

– በውጭ አገራት በተሰጡ የግልግል ዳኝነት ውሳኔዎች እውቅና የመስጠት እና የመፈጸም ስምምነትን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ ቁጥር 1184-2012

– የግልግል ዳኝነት እና የእርቅ አሰራርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታውቀዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here