በአዲስ አበባ የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሊጀመር ነው ተባለ

0
997

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ኦዲት እና ምዝገባ ሥራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። ምዝገባው ሕገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ያለመ መሆኑንም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ክንቲባ ኢንጂር ታከለ ኡማ የምዝገባ እና ኦዲት ሂደቱን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል። ከትናንት አርብ ነሐሴ 1/2012 ጀምሮ መካሄድ የጀምረው የምዝገባ እና ኦዲት ሥራ፣ ከመሃል ከተማ እስከ ዳር የአርሶ አደሮች ይዞታን ጭምር ያካተተ መሆኑም ተገልጿል።
በተለይም ለሕገወጥ ወረራ ተጋላጭ የሆነው የአርሶ አደሮች ይዞታን በመመዝገብ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲኖራቸው እንደሚደረግም ነው ያስታወቁት። ምዝገባው በቴክኖሎጂ አሰራር የተደገፈ እንዲሆን ከሳይንስ እና ኢኖቬሺን ሚኒስቴር ጋር በጋራ የሚሠራ መሆኑም ተጠቁሟል። አምስት ክፍለ ከተሞች ላይ የሚገኘው የአርሶ አደሮች መሬት ምዝገባም እስከ መስከረም 30 እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ምዝገባው በተለይም አርሶአደሮች በደላላ ተታለው ያለአግባብ መሬታቸው እንዳይወሰድ እና በሕገወጥ መንገድ እንዳይወረር ለመከላከል እንደሚረዳ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ በተለያዩ ጊዜያት ሕገ ወጥ የመሬት ወረራ እየተስፋፋ መሆኑ በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙኀን ሲነገር የቆየ ጉዳይ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 92 ነሐሴ 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here