ትውልደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካን ፕሬዚደንታዊ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

0
777

በአሜሪካ የሳቫና ስቴት ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ፕሮፌሰር የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሙላቱ ለማ (ዶ/ር) የአሜሪካን ፕሬዚዳንታዊ የሳይንስ፣ የሒሳብ እና የምሕንድስና የልህቀት ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገለጸ።
ሙላቱ ትምህርታቸውን ኢትዮጵያ እንደ ጀመሩ እንዲሁም የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን በአፕላይድ ማቲማትክስ ሀገራቸው ውስጥ እንዳገኙ ተገልጿል።
ወደ አሜሪካ ካቀኑ በኋላም እ.አ.አ በ1993 በፒዩር ማቲማቲክስ ማስተርስ እንዲሁም በ1994 በዚሁ ትምህርት ሦስተኛ ዲግሪ (ዶ/ር) ማግኘታቸውም ተነግሯል።
ሙላቱ(ዶ/ር) እ.አ.አ በ2011 በስማቸው የተሰየመ “የሙላቱ ቁጥር” የተሰኘ የሒሳብ ቀመር ለዓለም ማስተዋወቃቸው የተገለጸ ሲሆን በሳቫና ስቴት ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እየሠሩም ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ሙላቱ ከ100 በላይ የምርምር ጥናቶችን ማዘጋጀታቸውም የተነገረላቸው ሲሆን በሥራቸውም በተለያዩ ጊዜያት በርከት ያሉ ሽልማቶችን ማግኘታቸው ተጠቁሟል።

ቅጽ 2 ቁጥር 93 ነሐሴ 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here