ጉዳት የደረሰባቸው የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጥገና በቅርቡ እንደሚጀመር ተገለጸ

0
522

ከ900 ዓመታት በላይ ዕድሜን ያስቆጠሩት የቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲናት በእድሜ ብዛት፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮአዊ ችግሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ቅርሶቹን በየዘመናቱ ለመጠገን የተደረገው ጥረት ችግራቸውን ከመፍታት ይልቅ ለበለጠ ጉዳት እንደዳረጋቸው ተመላክቷል፡፡

ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱን ለመጠገን በ2012 ስራ መጀመሩ የሚታወስ ቢሆንም በአለምና በአገር ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የጥገና ስራው ተጓቶ መቆየቱን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኢትዮጵያና ፈረንሳይ ቅርስ አድን ፕሮጅክት የኢትዮጵያ አስተባባሪ የሆኑት ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ቅርሶቹን ለመጠገን ሙከራ ቢደረግም በተደራጀ የጥናትና ምርምር ስራ ያልታገዘ ስለነበር ውጤታማ አልነበረም ያሉት አስታባበሪው በ2012 የጥገና ስራውን ለማከናወን ስራዎች ቢጀመሩም በወቅቱ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ስራው ቆሞ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

አሁን ስራውን የሚሰሩ ባለሙያዎች መምጣታቸውንና ስራው መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ የቅርስ ጥገናው በኹለት ዘርፍ የሚካሄድ መሆኑንና የመጀመሪያው ዙር የቅርሱን ጉዳት በጥልቀት ማጥናትና ማወቅ ሲሆን ይሄም በዚህ ዓመት ይገበደዳል ያሉት ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ (ዶ/ር) ኹለተኛው ዙር የቅርስ ጥገናው የሚካሄድበት ሲሆን በዚህ የጥገና ሂደት ኹለት ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን አንደኛው ቅርሶቹ የተጎዱ በመሆናቸው ቅርሶቹን ማከም ነው፡፡

ኹለተኛው መጠለያው ጊዜያዊ በመሆኑ እና የአገልግሎት ጊዜው በማለፉና ሌሎች ችግሮች እንዳሉበት የሚስተዋል በመሆኑ መጠለያውን አንስቶ ሌላ መስራት ነው ብለዋል፡፡

ኹለቱንም ስራዎች ለማስኬድ በጥናትና ምርምር የታገዘ ስራ እንደሚካሄድ የገለጹት መንግስቱ ማህበረሰቡ የቅርሱ ጥገና በፍጥነት እንዲጀመር እያነሳ ያለው ጥያቄ ተገቢ ቢሆንም ‹‹የበሽታው ምንክያት ካልታወቀ የሚታዘዘው መድሃኒት በቅርሱ ላይ የሚያመጣው የጎንዮሽ ጉዳት የከፋ በመሆኑ›› መቸኮል እንደማያስፍልግ ጠቁመዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here