በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ 37 ሚሊዮን ብር ከደን ምርት ዝውውር ሮያሊቲ መሠብሰቡ ተገለጸ

0
717

የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን በበጀት አመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን አስመልክቶ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፍቃዱ በየነ(ፕ/ር) እንዳሉት በሩብ ዓመት ብቻ 37 ሚሊዮን ብር ከደን ምርት ዝዉዉር ሮያሊቲ ተሰብስቦ ለመንግስት ገቢ መሆኑን አስታውቀዋል። በሩብ በጀት ዓመቱ በየዘርፉ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካካል ሁሉም የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት የሚያስፈልጋቸው የልማት ፕሮጀክቶች ጥናቱን ሳያስጠኑ ወደ ልማት ሥራ እንዳይሸጋገሩ ለማድረግ ሰፊ ጥረት የተደረገ ሲሆን 1426 የልማት ፕሮጅክቶች በሩብ ዓመቱ የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ይሁንታ አግኝተው ወደ ሥራ መግባታቸውን አስታውቀዋል።

የአካባቢ ብክለት በቀጥታ በዜጎች ላይ የሚያስከትለው የማህበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ታሳቢ እንዲሁም ብከለትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሁሉም ዜጋ ድርሻ ወሳኝነት መነሻ ጥቆማ የማቅረብ እንዲሁም አስረጂነት ሳያስፈልግ በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ መመሰረት የሚችሉበት የህግ ሥርዓት ዝግጅት ተከናውኗል።
በማህበረሰቡ የብክለት ይወገድልኝ አቤቱታ ጥቆማዎች መነሻ የብክለት ምንጮችን ተለይተዉ 237 የብክለት ይወገድልኝ አቤቶታዎች በተለያየ ደረጃ ምላሽ እንዲያገኙ ተደርጓል።

የአካባቢ እንክብካቤ ሥራዎች አንዱ መሳሪያ ለሆነው የአካባቢ ይሁንታ ፈቃድ ቃድ 63 ልዩ ልዩ የሙያ እና ይሁንታ ፈቃዶች ተሰጥተዋል።
አገራዊ የደንና የጥበቃ ቦታዎች ሽፋንን ከማሳደግ ረገድ በጠቅላይ ሚኒስትራችን አመራር ሰጪነት በተደረገዉ ርብርብ ባሳለፍነዉ ክረምት 5 ቢሊዮን ችግኝ የተተከለ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 3 ነጥብ 562 ቢሊዮን የደን ችግኞች በ 771,795.66 ሄክታር መሬት ላይ መተከላቸውን እና ከእዚህም ውስጥ 31 በመቶ የሚሆኑት የሀገር በቀል ዝርያዎች እንደሆኑ አንስተዋል ።

ለተተከሉት ችግኞች የእንክብካቤ ተግባራትን አስመልክቶ የአረምና የኩትኳቶ ስራ እየተከናወነ ሲሆን በነሀሴ ወር መጨረሻም በሞቱት ችግኞች የመተካት ተግባር ተከናዉኗል።

በዚህ በጀት ዓመት ለጎረቤት አገሮች የሚደረገዉን ድጋፍ ጨምሮ 6 ቢሊዮን ችግኝ የሚዘጋጅ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 4 ቢሊዮን የደን ችግኝ የማፍላት ቅድመ ዝግጅት እየተካሄደ ሲሆን በዚህ ሩብ ዓመት ለዚሁ ተግባር የሚዉል 31 ነጥብ 3 ቶን የተለያዩ የዛፍ ዝርያ ዘሮችን በማሰባሰብ እንዲሰራጭ ተደርጓል።
ያሉንን የተፈጥሮና ሰዉ ሰራሽ ደኖቻችንን ከመጠበቅ ረገድ17ነጥብ 22 ሚ/ሄ/ር ነባር የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ደኖችን የመጠበቅ፣ የመንከባከብና በዘላቂነት እንዲጠበቅ የማድረግ ስራ ተሰርቷል።

በተጨማሪ 0 ነጥብ 457 ሚሊዮን /ሄ/ር መሬት ላይ የሚገኙ የተፈጥሮ ደኖችን በአሳታፊ የደን አስተዳደር ስርዓት በማስገባት በዘላቂነት እንዲጠበቁና ተገቢውን ግልጋሎት እንዲሰጡ ተደርጓል። ከደን ዘርፉ የሀብት ግኝትን በማሳደግ ረገድ 37 ሚሊዮን ብር ከደን ምርት ዝዉዉር ሮያሊቲ ለማግኘት ለማሰባሰብ ተችሏል።
በተጨማሪም 59 ሺ ቶን የደን ምርት ዉጤቶችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለ ሲሆን ወደ ውጭ ከተላከ እጣንና ሙጫ 611,059 የአሜሪካ ዶላር ማገኘት ተችሏል።

በዘርፉ ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ለ320 ሺ ዜጎችን ጊዜያዊ የስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ 140,071 ሴቶች ናቸዉ። የሀገራችን ፍላጎትና አቋም የሚያሳዩ ኹለት የአካባቢ ስምምነት ሰነዶችን ተዘጋጅተው ለሴክሬታሪያቱ ተልከዋል።

በኹለት የዓለም አቀፍ የአካባቢ ስምምነቶች ድርድር መድረኮች እና በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ ተሳትፎ በሚደረግባቸው ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጉዳይ ስብሰባዎችና ፎረሞች ለመሳተፍና የሀገራችን ፍላጎት እንዲንጸባረቅ ተደርገጓል።

ቅጽ 2 ቁጥር 103 ጥቅምት 14 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here