10ቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ያላቸው የአፍሪካ አገራት

0
1977

ምንጭ፡-የአፍሪካ ንግድ ሪፖርት 2018

በባለፈው ዓመት፤ የበርካታ አፍሪካ አገራት የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከፍተኛ ጭማሪ ኣሳይቶ ነበር። ለዚህም እንደ ዋነኛ ምክንያት የተገለጸው የዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር እና የአገራቱ የውጭ ንግድ ገቢ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ነው። በቁጥር ለማስቀመጥ ያህል፤ የሁሉም አፍሪካ አገሪት የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ 6 ነጥብ 3 በመቶ በመጨመር 421.5 ቢሊየን ዶላር በባለፈው ዓመት የደረሰ ሲሆን አልጄሪያ፣ ሊቢያ እና ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ አገራት ሆነዋል።
ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቶጎ አነስተኛ የውጭ ምንዛሬ በማስመዝግብ ቀዳሚ ሆነዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ፤ ወደ 3 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ክምችት በማስመዝገብ ከነዚህ አገራት የተሻለ ደረጃ ብትገኝም፤ መጠኑ ግን ከ 1 ወር ከ18 ቀናት የገቢ ንግድን የዘለለ መሸፈን አይችልም። በዚህም የተነሳ፤ ብዙ በንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በታች እንዲሰሩና ገቢያቸው እንዲያሽቆሎቁል ምክንያት ሆኗል። ለትይዩ ገበያው መስፋፋትም ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።

ቅጽ 1 ቁጥር 8 ታኅሣሥ 27 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here