የኢትዮጵያን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ወደ ኢትዮሳት ሊዞሩ ነው

0
838

የኢትዮጵያ አብዛኞቹ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከታህሳስ 23 / 2013 አመት ጀምሮ ወደ 57 ዲግሪ ምስራቅ ሙሉ በሙሉ እነደሚዞሩ ተገልጻል።
የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ተመልካቾች አብዛኛዎቹን ተወዳጅ ጣቢያዎቸ ከታህሳስ 23/ 2013 ጀምሮ በ57 ዲግሪ ምስራቅ በኢትዮሳት ላይ ብቻ ያገኛሉ።
ማክሰኞ ታህሳስ 6 / 2013 በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ የቴሌቪዥን ተመልካቾች ኢትዮሳትን ለማግኘት ባቅራቢያቸው የሚገኙ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻኖችን በመጥራት የሳተላይት ዲሻችውን ማዞር ይኖርባቸዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ መንግስትን፥ የህዝብ እና የግል ብሮድካስተሮችን በመወከል ዓለም አቀፍ የይዘት ግንኙነት አገልግሎት አቅርቦት ቀዳሚ ስፍራ ከሚይዘው ኤስ.ኢ.ኤስ ጋር የተፈራረሙት የአጋርነት ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያዊ ይዘት ያላችው ፕሮግራሞች በአንድ የቴሌቪዥን ሰፈር በቋሚነት መገኘትና መጠናከር በሃገሪቱ አዲስ ምዕራፍ መጀመሩን አብስሯል።
የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውና በኤን.ኤስ.ኤስ-12 ሳተላይት የሚስራጨው ኢትዮሳት ነፃ የቴሌቪዥን አገልግሎት መድረክ ሲሆን። ኢትዮሳት በጥቅምት ወር 2011 በኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና በኤስኢኤስ አማካኝነት ስራውን ያስጀመረ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ለማጠናከርና ተመልካቾች ቁጥራቸው ከፍ ያለ የውጪ ጣቢያዎቸ መካከል ሳይማስኑ በአንድ ቦታ ከአንድ ምሕዋር እንዲያሰራጩ ለማስቻል የተደረገ ስምምነት ነበር።
የብሮደካስት ባለስልጣን፥ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ኤስ.ኢ.ኤስ በጋራ በመሆን በ’ኢሊቬት’ ዓለማቀፍ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻኖች ስልጠና 20 ሺህ ወጣቶችን በማሰልጠን በመላ ሃገሪቱ ወደ ስራ ለማስገባት እየተሰራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ(ዶ/ር) እንደተናገሩት “አብዛኛዎቹን የኢትዮጵያ የሳተላይት የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ወደ አንድ ቦታ በማዛወር የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጠቅምና በእርግጥም ኢትዮጵያዊ ብቻ የቴሌቪዥን አቅርቦትን ፈጥረናል ብለዋል። ከተለያዩ የብሮድካስቲንግ ማህበራት እና ከ SES ጋር በመሆን በመላ አገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የቴሌቪዥን ባለቤት ኢትዮጵያውያን ጥራት ያለው ይዘት ማግኘታቸውን እንዲቀጥሉ እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ ሳተላይት አቅጣጫ እንዲያስተካክሉ ለማገዝ እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ በበኩላቸው “ከኤስ.ኢ.ኤስ ጋር በኢትዮሳት ላይ ሙሉ በሙሉ አዲስ የቴሌቪዥን ልምድን የሚያመጣ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለማድረግ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል።” ብለዋል ። “ይህ ትብብር በተጨማሪ በኢትዮጵያ ያለውን የህዋ ዘርፍ ለመደገፍ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ሲሆን ይህ ለኢትዮጵያውያን በልዩነት የቀረበው የቴሌቪዥን መድረክ ለኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ብሩህ ተስፋን እንደሚጭር እምነት አለን” ሲሉም ተናግረዋል።
የኤስኢኤስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ስቲቭ ኮላር በበኩላችው “ኤስ.ኢ.ኤስ እንደዚህ ባለ ላቅ ያለ ፕሮጀክት ውስጥ ወሳኝ ሚና በመጫወቱ ኩራት ይሰማዋል ፣ ቀሪ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ወደ ኢትዮሳት የሚያደርጉት ዝውውር ያለ ምንም ችግር እንዲካሄድ በቁርጠኛ እንሰራለን። ሽግግሩን ውጤታማ ለማድርግ እያንዳንዱን የቴሌቪዥን ቤት ጥራት ያለው የዲሽ ማዞር አገልግሎት እንዲያገኝ የሳተላይት ገጠማ ሥልጠናው አጠናክሮ በማስቀጠል እና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተመልካቾችን እርካታ ለማስጠበቅ እንሰራለን ” ብለዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 112 ታኅሣሥ 17 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here