ዳሰሳ ዘማለዳ ዓርብ መስከረም 2/2012

Views: 381
  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ አራተኛ መዳረሻውን በመጪው ታኅሳስ ወር ላይ ወደ ሒውስተን ቴክሳስ እንደሚጀምር አስታወቀ። በረራው ከአዲስ አበባ በቶጎ ሎሜ ወደ ሒውስተን የሚደረግ ይሆናል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………

  • በኢንፎርሜሽ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም ሹመት የነበረው የመካከለኛ ደረጃ ኃላፊነት ምደባ በውድድር እንዲሆን ማድረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል። ሰራተኞች በፈለጉበት ቦታ መስራት የሚችሉበትንም አሰራር መፍጠሩን ያለፈውን ዓመት ኤጀንሲው ያከናወናቸውን ተግባራት በገመገመበት ወቅት ገልጿል። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………….

  • በአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ የሚመራው ግብረ ኃይል ጷጉሜ 5 እና 6/2011 ሕገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ባደረገው ድንገተኛ ቁጥጥር ሠላሳ አይሱዙ ተሽከርካሪዎች የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ያለ ደረሰኝ ሲሸጡ እጅ ከፍንጅ መያዙን አስታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………..

  • በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለቤላሩስ ፕሬዘዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ አቀረቡ። አምባሳደሩ ከሩሲያ ፌደሬሽን በተጨማሪ በቤላሩስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለግላሉ። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………….

  • አገር አቀፍ የዐስረኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይፋ ሆኗል። በውጤቱም 75 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ተፈታኞች ኹለት ነጥብ እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል። 10ሽሕ የሚሆኑት ደግሞ 4 ነጥብ አምጥተዋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………

  • የጎንደር ዩኒቨርስቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የግዕዝ ቋንቋን በዲግሪ መርሃ ግብር መስጠት ይጀምራል። (አብመድ)

……………………………………………………….

  • 1መቶ 99 የሚሆኑ የየካቲት ወረቀት ስራዎች ድርጅት ሰራተኞች ያለ ፈቃዳችን ወደ ሌላ የሥራ ቦታ እንድንዘዋወር ተደርገናል ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። ድርጅቱ ያጋጠመውን ኪሳራ ተከትሎ ሀይ ቴክ ፓኬጂንግ ወደተባለ እህት ኩባንያ እንዲዘዋወሩ ማድረጉን ገልጿል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

…………………………………………………….

  • ኢትዮጵያ 258 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ቀዳሚ መሆኗን ኤዋይ የተሰኘ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አማካሪ ተቋም ይፋ አደረገ። (ዋልታ)

……………………………………………………..

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com