25ኛ የምስረታ በዓሉን እያከበረ ያለው ዳሸን ባንክ በሴት የባንክ ባለሙያዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ በቦሌ አፍሪካ ጎዳና ኖክ ሕንጻ ላይ መክፈቱን አስታወቀ።
በቦሌ ኖክ ህንጻ ላይ የተከፈተው የመጀመሪያው ቅርንጫፍ ከ 15 በላይ የሚሆኑ ሴት የባንክ ባለሙያዎች እንዳሉት የታወቀ ሲሆን ባንኩ ካሉት ከ 10 ሺህ በላይ ከሚሆኑ ሰራተኞች መካከልም 30 በመቶ የሚሆኑት ሴት የባንክ ባለሙያዎች እንደሆኑ ታውቋል። በተጨማሪም 27 በመቶ የሚሆኑ ሴቶችም እንዲሁ በከፍተኛ የአመራር ሰጪ ኃላፊነት ቦታ ላይ እየሰሩ እንደሆነ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አስፋው ዓለሙ አስታውቀዋል።
“ ምንም እንኳን ብዙ መሥራት ቢቀረንም ሴቶችን ወደ አመራር ማምጣት የባንኩም የወደፊት አቅጣጫ በመሆኑ ቀጣይ ሥራዎች መስራት እንደሚገባቸው እናምናለን” ሲሉ አስፋው ተናግረዋል።
ዳሽን ባንክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ለባንክ ኢንዱስትሪው በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ የሆነው ባንኩ፣ ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን የኤሌክትሮኒክ ክፍያ ካርድና(ኤቲኤም) እንዲሁም የባንክ መረጃን በአንድ ቋት መስራትን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።
በ50 ሚሊየን የተፈቀደ ካፒታል እና 10 ቅርንጫፎች ስራውን የጀመረው ዳሸን ባንክ አሁን ላይ 450 ቅርንጫፎች 10 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን ከ2.5 ሚሊየን በላይ ደምበኞችን አፍርቻለሁ ብሏል።
በአሁኑ ጊዜ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ወደ ሰባ ቢሊዮን ብር የተጠጋ ሲሆን ፣ ይህም በኢንዱስትሪው ከግል ባንኮች ሁለተኛ ከፍተኛ የሀብት መጠን ያለው ባንክ ያደርገዋል።
ባንኩ ሥራ የጀመረው በ50 ሚሊዮን ብር ካፒታልና በአሥር ቅርንጫፎች ነው። በአሁኑ ሰዓት የቅርንጫፎቹን ቁጥር 450 አድርሷል። የባንኩ አስቀማጮች ቁጥር ደግሞ 2.5 ሚሊዮን መድረሱ ታውቋል።
“በብዙኃን መገናኛዎቹ የተስተዋለው ፓርቲ ውግንና ዝንባሌ “ በሚቀጥሉት ጊዜያት በሚኖረው ነፃና ፍትሃዊ የምርጫ አዘጋገብና የምርጫ መረጃ ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳይኖረው ስጋት አለን”
ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013



