ለቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ስምንት ሺሕ 209 እጩዎች መመዝገባቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

0
420

የኢትዮጵያ ብሐየራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 2/2013 የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መገለጫ ስምንት ሺሕ 209 እጩዎች መመዝገባቸውን አስታውቋል፡፡
47ቱ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 8209 እጩዎች አስመዝግበዋል። ከፍተኛ እጩ ካስመዘገቡ ፓርቲዎች መካከል የመጀመሪያው ብልፅግና ፓርቲ ሲሆን ኹለት ሺሕ 432 እጩዎች አስመዝግቧል፣ ኸለተኛው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሲሆን፣ አንድ ሺሕ 385 እጩዎች አስዝግቧል፡፡ ሦስተኛው ደግሞ እናት ፓርቲ ሲሆን 573 እጩዎች አስመዝግቧል ተብሏል፡፡
ሁሉም ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች 49 ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ውስደዋል። ምርጫ ምልከት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል።
በአጠቃላይ እጩ ካስመዘገቡት 47 ፓርቲዎች ውስጥ አራት ለክልል ኹለት ደግሞ ለፓርላማ የሚወዳደሩ ናቸው። 125 እጩ ተወዳዳሪዎች በግል ተመዝግበዋል። በእጩዎች ምዝገባ ወቅት ችግሮች እንዳጋጠሙት በርዱ ጠቁሟል፡፡ በዚሁ መሰረት ከ16 በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታዎችን አቅርበው መፍትሄ እንደተሰጣቸው ነው የተመላከተው፡፡
በእጩዎች ምዝገባ ላይ ያጋጠሙ ማለትም አስፈፃሚዎች የሌሉባቸው ቦታዎች፣ የምርጫ ክልል ቢሮዎች መክፈት መዘግየት፣ በየወረዳው ተዘዋውሮ እጩዎችን ለማስመዝገብ የፀጥታ ችግርንና ሌሎችም ችግሮች እንደነበሩ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት የምረጡኝ ዘመቻ አድራጊዎቹን ለአጭር ጊዜ መያዝ፣ የወረዳ ሃላፊዎችን የማስፈራራት፣ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም የሚል ማስታወቂያ መለጠፍና የመሳሰሉት ችግሮች እንደነበሩም ገልጸዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እጩዎቻቸውን ያላስመዘገቡ ፓርቲዎች ናቸው።


ቅጽ 2 ቁጥር 123 መጋቢት 3 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here