ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

0
679

ዳያስፖራው በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ለጉዳት ለተጋለጡ ዜጎች ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከዳያስፖራው ከ236 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ሀብት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ለሚከናወኑ ስራዎች መሰብሰቡንም ገልጿል።
መንግሥት በጥቅምት ወር “የሕወሓት ቡድን” በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል።
በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በተከሰቱ የጸጥታ ችግሮችና በንጹሃን ዜጎች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ዜጎች ለችግር እየተጋለጡም መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ዳያስፖራው ለተቸገሩ ወገኖችና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተቋማት ድጋፍ ማሰባሰብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳብ ማቅረቡን ገልጸዋል።


ቅጽ 3 ቁጥር 131 ሚያዚያ 30 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here