አውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ምርጫ መታዘቡን ሰረዘ

0
550

የኅብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል አውሮፓ ኅብረት ታዛቢዎች እንዲልክ በማሰብ ለመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ አስፈላጊ ናቸው በተባሉ ቁልፍ መስፈርቶች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት ለመድረስ ጥረት ሲያደረግ ቢቆይም ሥምምነት ላይ መድረስ አልተቻለም ብለዋል።
በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምርጫውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ሁኔታዎች አልተሟሉም። ስለዚህም የታዛቢ ልዑክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊያደርግ የነበረውን ስምሪት ሰርዟል ነው ያሉት፣ የኅብረቱ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦሬል።
ማንኛውም የምርጫ ታዛቢ ቡድን ሊያሟላቸው የሚገቡ ነገሮች ማለትም የልዑኩ ነፃነት እና የደኅንነት ስጋቶች በሚኖሩበት ጊዜ የልዑኩ የግንኙነት ስርዓቶች እንዲሁም ልዑኩ የሚጠቀምባቸው የደኅንነት ቁሳቁሶች ማስመጣት የመሳሰሉ መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ የኢትየጵያ መንግስት ባለመፈቀዱ የአውሮፓ ኅብረት ቁጭት ይሰማዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ምርጫ ታአማኒ፣ አካታችና ግልጽ ምርጫ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የ20 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ ማድረጉን አውሮፓ ኅብረት አስታውሷል።


ቅጽ 3 ቁጥር 131 ሚያዚያ 30 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here