ምርጫዬ የተሰኘው የምርጫ መቀስቀሻና የመረጃ አገልግሎት መስጫ መተግበሪያ ሥራ ላይ ዋለ

0
449

ኢትዮጵያ ለስድስተኛ ጊዜ አገራዊ ምርጫ ለማከናወን እየተሰናዳች ትገኛለች። የዘንድሮ የምርጫ ሂደት በዘመነኛ የምርጫ ቅስቀሳ እና የምርጫ መረጃዎች ስርጭት ይታገዝ ዘንድ የወጠነ አገር በቀል ተቋም አዲስ የስልክ መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።
“ምርጫዬ” የተባለው በእጅ ስልክ ላይ የሚጫን መተግበሪያ፣ መራጮች የተጣሩ ምርጫ ነክ መረጃዎችን እንዲያገኙ ከማገዝ በተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕቅዶቻቸውን የሚያጋሩበት እና የምረጡኝ ዘመቻቸውን የሚከውኑበት አማራጭ ይሆን ዘንድ እንደተዘጋጀ ተነግሯል።
መተግበሪያውን ያሰናዳው እውነት የተሰኘ የተግባቦት ተቋም ሲሆን ፣ የምርጫዬ መተግበሪያ ፋይዳ ማንኛውም ሰው የተረጋገጡና ከምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን በአንድ ላይ ማግኘት ማስቻል ነው ተብሏል።
የምርጫዩ መተግበሪያ ይዘትን ለማወቅ አዲስ ማለዳ መተግበሪያውን ሞክራ እንዳረጋገጠቸው የሚወጡት መረጃዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማንፌስቶና አድራሻ ያካተተ ነው።


ቅጽ 3 ቁጥር 132 ግንቦት 7 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here