ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጨማሪ የምርጫ ጣቢያ ከፈተ

0
705

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ያለውን የመራጮች ምዝገባ ጣቢያዎች እጥረት ለማስተካከል እየሰራ እንደሆነ ገልጿል። በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተጨማሪ ጣቢያዎች በመክፈት የቀሩት የመራጮች ምዝገባ ቀናት የተሻለ ምዝገባ እንዲካሄድ ጥረት እያደረግሁ ነው ብሏል።
በየካ አባዶ ኮንዶሚኒየም የተከፈቱ አዲስ ምርጫ ሰባት፣ የካ ሃያት ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያ አንድ፣ ቦሌ አራብሳ ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያ አንድ፣ ጀሞ ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች ዘጠኝ (ጀሞ በተጨማሪ መከፈት የነበረባቸው ስድስት አዲስ ምርጫ ጣቢያዎች ወረዳው መስተዳድር ቦታ ባለማዘጋጀቱ ምክንያት እስካሁን ሊከፈቱ አልቻሉም።) ሲል ቦርዱ አስታውቋል። ቱሉ ዶምቱ ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች አምስት፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ሶስትና ገላን ኮንዶሚኒየም አዲስ የተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች አምስት መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል።
በልዩ ሁኔታ በተለይ በጀሞ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምርጫ ጣቢያዎችን ለመክፈት ለከተማ መስተዳድሩ በተደጋጋሚ ቦርዱ ቢያሳውቅም ከወረዳው ቢሮዎችን ማዘጋጀት ባለመቻሉ ከታቀዱት 15 አዳዲስ ጣቢያዎች ስድስቱን መክፈት አለመቻሉን በመጥቀስ፣ ችግሩን ለመፍታት እየሰራሁ ነው ብሏል።
በዚህ መሰረት አዲስ በተከፈቱት ጣቢያዎች መራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ የጠቆመው ቦርዱ፣ ችግሮችን ሪፓርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመራችን 778 በመደወል አሳውቁኝ ብሏል።


ቅጽ 3 ቁጥር 132 ግንቦት 7 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here