የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳሳወቀው በሶማሌ ክልል በ11 የምርጫ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ ላይ ታይተዋል የተባሉ ጉልህ የአሰራር እና የሕግ ጥሰቶችን የማጣራት ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ገልጿል። በዚህም መሰረት ቦርዱ አምስት በሕግ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ ሲቪል ማኀበራትን በማጣራት ሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ ያደረገ ሲሆን፣ በሂደቱም ሦስት ማኀበራት በዚህ የማጣራት ሥራ ላይ የሚሳተፉ የሕግ ባለሙያዎችን መመደባቸው ተጠቁሟል።
ቦርዱ 10 አጣሪ ቡድኖች (ከቦርዱ የኦፕሬሽን ባለሙያ፣ የሕግ ባለሙያ እና አስተርጓሚ የተወጣጡ) አዘጋጅቶ 9 ያሰማራ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በ10 የምርጫ ክልሎች የማጣራት ሥራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ። በሚቀጥሉት ቀናት ከጌላዲን ምርጫ ክልል ውጪ በማጣራት ሂደቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መራጮችና የቀረቡ ሠነዶችን እንደሚመረምሩ ተጠቁሟል።
ቅጽ 3 ቁጥር 134 ግንቦት 21 2013


