የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመንግሥት ሠራተኞችን አሳሰበ

0
649

በዝቅተኛ የመንግሥት እርከን ላይ የሚገኙ ሠራተኞች ምርጫ ጣቢያ ላይ ያለምንም ከቦርዱ የሚሰጥ የፓርቲ ወኪልነትን የሚያሳይ መታወቂያ ወጭ በመገኘት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መረጃ በመጠየቅ እና በአንዳንድ ኹኔታዎች የመራጮች መዝገብን ለመጎብኘት እና መረጃዎችን ለመውሰድ ጥረት በማድረግ ጣልቃ መግባታቸውን ቦርዱ ተረድቻለሁ ብሏል።
ኹኔታው በተለይ ወደ ድምጽ መስጫ ቀን እየተጠጋን በመጣን ጊዜ የምርጫ ሂደቱን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያውክ ከመሆኑም በላይ በምርጫ ሕጉም ሆነ በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተቀመጠ ወንጀል እንደሆነ ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥድስተኛው አጠቃላይ ምርጫን ተግባራት እያከናውነ ቆይቶ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁ እና የመራጮች መዝገብ ይፋ ማድረጉን ጠቁሟል። የመራጮች ምዝገባ ሂደት ከሞላ ጎደል በስኬታማነት የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ ሂደቱ እየተከናወነበት ካለበት ጊዜ አንስቶ የሚታዩ በተለይ የዝቅተኛ የመንግስት እርከን ሰራተኞች(ወረዳ፣ ቀበሌ፣ወዘተ.) ጣልቃ ገብነቶችን በተለያየ መንገድ ለሚመለከታቸው አካላት ሲያሳውቅ ቆይቷል።
በቅርቡም ቦርዱ በግንባር ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ፣ በነጻ የስልክ ጥሪ መስመር የሚመጡ ጥቆማዎችን በመከታተል፣ የክትትል ቡድኑን በማሰማራት የምዝገባ ሂደቱን ለመገምገም መሞከሩን ጠቁሟል።


ቅጽ 3 ቁጥር 134 ግንቦት 21 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here