የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ምርጫውን አስመልክቶ ስለሚጫወቱት ሚና ምክክር ተካሄደ

0
722

የኃይማኖት አባቶች እና የአገር ሽማግሌዎች 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ፍትሐዊ ፣ሠላማዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚጫወቱትን ሚና በተመለከተ በጅማ ከተማ ምክክር መካሄዱ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር 6ኛው አገራዊ ምርጫ ፍትሐዊ ፣ሠላማዊ እና ተአማኒ እንዲሆን የኃይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎች ስለሚጫወቱት ሚና የሚዳስስ የምክክር መድረክ መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን 17 ወረዳዎች እና ከጅማ ከተማ የተውጣጡ የኃይማኖት አባቶች ፣የአገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በውይይት መድረኩ እንደተሳተፉ ታውቋል። ለሦስት ቀናት በቆየው መድረክ ላይ የአብሮነት እና የሠላም እሴትን የሚያጎለብቱ አጀንዳዎች እንደተነሱ ተነግሯል።


ቅጽ 3 ቁጥር 136 ሠኔ 5 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here