ኢንጅነር እንብዛ ታደሰ የተባለ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣን ከቀናት በፊት አሸባሪ ተብለው በተፈረጁት የህወሓት ታጣቂዎች ከመቐለ ታፍኖ ተወስዶ በሚያሳቅቅ መንገድ ተገድሎ በመቐለ ትልቁ ውህኒ ቤት አካባቢ አስክሬኑን ጅብ በልቶት ተገኝቷል።
እንብዛ MIT የተመረቀ ምጡቅ አዕምሮ የነበረው ወጣት ነው። እንብዛ በINSA ለብዙ አመት ለአገሩ አገልግሏል፡፡ ከመገደሉ አስቀድሞ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሁኖ ሕዝቡን እያገለገለ ነበር።
ወጣት ኢንጅነር እንብዛ ጥሩ አርቲስትም የነበረ ሲሆን፣ ኹለት ትግርኛ ዘፈኖች የነበሩት እና ሥራዎቹ በሕዝብም ዘንድ ተቀባይነት ነበራቸው። እስካሁን 30 የሚሆኑ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር አመራሮች በአሰቃቂ መንገድ በህወሓት ተገድለዋል። ኢንጆነር እንብዛ ባለትዳር እና የኹለት ልጆች አባት ነበር። ግዕዝ ሚዲያ እንደዘገበው በትግራይ ያሉ የጊዚያዊ አስተዳድሩ አመራሮች ራሳቸውን ከአደጋ የሚከላከሉበት ሽጉጥ እንኳ መንግሥት አልሰጣቸውም።
ቅጽ 3 ቁጥር 138 ሠኔ 19 2013


