የኮቪድ- 19 ክትባትን ኢትዮጵያ እና እስራኤል በጋራ ሊያመርቱ ነው

0
644

ኢትዮጵያ እና እስራኤል የኮቪድ- 19 ክትባትን በጋራ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊያመርቱ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በጤናው ዘርፍ አብሮ ለመስራት ያተኮረ ውይይት ያደረጉት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ፣ ምክትል አምባሳደር ኦር ዳንኤሊ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ክትባቱን እንዴት በጋራ ኢትዮጵያ ውስጥ ማምረት እንደሚቻል መነጋገራቸው ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ እና እስራኤል በኢትዮጵያ የኮቪድ- 19 ክትባትን በጋራ ለማምረት የሚችሉበትን ሁኔታ፣ የአቅም ግንባታ፣ የጤና ዘርፍ ኢንቨስትመንት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በኹለቱ አገራት ጤና ሚኒስቴር መካከል ትብብር ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት መደረጉ ተነግሯል፡፡


ቅጽ 3 ቁጥር 139 ሠኔ 26 2013

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here