ፖሊስ የዘመነ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሊታጠቃቸው የሚገባቸውን ትጥቆች የሟሟላት ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ

0
642

ፖሊስ የዘመነ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሊታጠቃቸው የሚገባቸውን ትጥቆች የሟሟላት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፋንታ ገለፁ፡፡

ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ ይህንን የገለፁት በትላንትናዉ እለት ለበርካታ አመራሮች በተሰጠዉ የራዲዮ መገናኛ አጠቃቀም ስልጠና ላይ ነዉ፡፡

ተቋሙ በርካታ ወጪ በማውጣት ሰራዊታችን የሚገለገልበትን ራዲዮ በአዲስ መልክ የመቀየር ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

የፖሊስ ስራ ሙያ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ ስራ ነዉ ያሉት ኃላፊው ህብረተሰቡ ከፖሊስ የሚጠብቀዉን አገልግሎት በተሟላ ማግኝት እንዲችል ተገቢዉን ስልጠና ለሰራዊቱ በመስጠት ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት መከላከል የሚያስችል አቅምን መፍጠር ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ኮሚሸነር ጄነራሉ አክለውም ፖሊስ ሊታጠቃቸው ከሚገቡ ትጥቆች ዋነኛውና ትልቁ የራዲዮ መገናኛ መሆኑን በመግለፅ ተቋሙ ዲጂታል የሞቶሮላ ራዲዮ መገናኛን የመጠቀምና የማስፋፋት ስራ ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሸለና እያደገ በመሆኑ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል የራዲዮ መገናኛ በመሸጋገር ሰራዊታችን በተፈለገ ቦታ የሚፈለገውን አገልግሎት በተቀላጠፈ መንገድ ለህብረተሰቡ መስጠት እንዲችል በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዓለም የደረሰበትን ደረጃ በመድረስ ከወቅቱ እድገት ጋር መጓዝ ያስፈልጋል ሲሉም ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት በዲጂታል የራዲዮ መገናኛ አጠቃቀም ዙሪያ ለአመራሮቹ በቂ ስልጠና መስጠቱም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here