አዲስ የሚመሰረተው ፓርላማ ውጤታማ እንዲሆን የሚያግዘው ጽ/ቤት ሊኖር ይገባል ተባለ

0
874

አዲስ የሚመሰረተው ፓርላማ ውጤታማ እንዲሆን የሚያግዘው ጽህፈት ቤት ሊኖር እንደሚገባ ተገለፀ።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።

በዚህ የምክክር መድረክ ላይ አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎና ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለን ጨምሮ የምክር ቤቱ እና የጽህፈት ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡

በመድረኩ ላይ አሁን ያለውን የጽህፈት ቤት አደረጃጀት በመከለስ አማራጭ የአደረጃጀት ጥናት በባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን÷ጥናቱ የህንድ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የቦትስዋና እና የእንግሊዝ ፓርላማ ጽህፈት ቤቶች ተሞክሮን የዳሰሰ ስለመሆኑ የጥናቱ አቅራቢዎች ገልጸዋል፡፡

እንደ ጥናቱ አቅራቢዎች ለሀገራችን ካለው አስፈላጊነት እንዲሁም አቅምን ባገናዘበ መልኩ የየሀገራቱን ልምድ በመቀመር የተዘጋጀው ይህ አደረጃጀት ምክር ቤቱን በማዘመን ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ያስችለዋል ተብሏል፡፡

የቀረበው የአደረጃጀት ጥናት የምክር ቤቱን ስራዎች በጥልቀት የዳሰሰ መሆኑና አሁን በስራ ላይ ያለውን የጽህፈት ቤት አደረጃጀት ክፍተቶች ለማቃናት እንደሚያግዝ በቀረበው ጥናት ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ከፍተኛ አመራሮች ጠቁመው፤ ጥናቱ ሊፈትሻቸው ይገባል ያሉትን ምክረ-ሃሳብም ሰንዝረዋል፡፡

የአደረጃጀት መዋቅሩ ብቻውን ውጤታማ እንደማያደርግና የሰው ኃይል አስተዳደሩና ፍትሃዊ የድልድል መመሪያ ማዘጋጀት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተገልጿል።

ም/ቤቱ የአደረጃጀት የጥናቱን ሂደት በቅርበት ሲከታተል እንደነበር የገለጹት የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአደረጃጀት ሰነዱ ለአስተያየት ክፍት እንደሆነና የተለያዩ ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንደሚዳብር መገለጹን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም የም/ቤቱ ጽ/ቤት ሰራተኞች በአደረጃጀት ሰነዱ ላይ ተወያይተው ተጨማሪ ግብኣት እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here